Fana: At a Speed of Life!

400 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳባሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ወር ውስጥ 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ ባህርና ሎጅስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ እንዳስታወቀው የአፈር ማዳባሪያ የማጓጓዝ ስራው በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በትናንትናው ዕለትም 50 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የጫነችው ሥድሥተኛዋ መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን ገልጿል፡፡

ጅቡቲ ከደረሰው አጠቃላይ የአፈር ማዳበሪያ 200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መሰራጨቱንም አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.