Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ተሀድሶ ምክር ቤት ኮሚሽን በቀጣይ ሊሰራቸው ባቀዳቸው ተግባራት ላይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተቋቋመውን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ድርጅታዊ መዋቅር እና ኮሚሽኑ በቀጣይ ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን ስራዎች አስመልክቶ ውይይት አድርጓል፡፡

የኢፌዴሪ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለሰላም ሚኒስቴር ሲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 565/2015 መቋቋሙ የሚታወስ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ዓላማ የተለያዩ ቡድን ተዋጊዎች ከማህበረሰቡ ጋር በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ እና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ በማድረግ፥ በሀገሪቱ የልማት የሰላምና የዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረግ ነው፡፡

ይሄው የብሔራዊ ተሀድሶ ምክር ቤትም በዛሬው ውይይቱ አዲስ የተቋቋመውን ኮሚሽን አደረጃጀት፣ መዋቅርና በቀጣይ ሊሰራቸው ባቀዳቸው ስራዎች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.