Fana: At a Speed of Life!

በቡራዩ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ ) ትናንት ምሽት 3:15 ላይ በሸገር ከተማ ቡራዩ በስፖንጅና በፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከባድ ጉዳት ደረሰ።

በሦስት የእሳት አደጋ ሠራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል።

በንብረት ላይ የደረሰው የውድመት መጠንና የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰባት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ፣ 2 የውኃ ቦቴ እና 60 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተሰማርተዋል።

አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 3:25 ደቂቃ ፈጅቷል።

እሳቱ ተስፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ መቻሉን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ፖሊስ ለጊዜው ያጠናቀረው ሪፖርት እንዳመላከተው ከ14 እስከ 15 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ወድሟል።

የገፈርሳ ቡራዩ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰይፉ ደምሴ እንደገለፁት፥ በሸገር ከተማ በቡራዩ ክፍለ ከተማ አኒዲማ ወረዳ የተከሰተው አደጋ ወደሌሎች አካባቢዎች ሳይዛመት በተደረገው ርብርብ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ተናግረዋል።

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.