የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ  ህገወጥ ይዞታዎችን እያፈረሰ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር ገለፀ

By Tibebu Kebede

April 06, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ወቅታዊ ሁኔታን ተገን በማድረግ የመሬት ወረራዎች እየታዩ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

በተለይም በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የመሬት ወረራው ታይቷል ነው ያለው።

የከተማ አስተዳደሩም ህገወጥ ይዞታዎችን እያፈረሰ ሲሆን በቀጣይም እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አስተዳደሩ የገለፀው።

ወቅታዊ ሁኔታ ተገን በማድረግ የሚደረጉ የመሬት ወረራዎችን ከማፍረስ በተጨማሪ ፈፃሚዎችና ተባባሪዎችን በህግ የሚጠይቅ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።