Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው 105 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለማህበራት አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ስራ እድልና ክህሎት ቢሮ ግብርናን ለማዘመን የሚያግዙ 105 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለ105 ማህበራት አስረክቧል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የቢሮው ሃላፊ ማቲዮስ ሰቦቃና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ መስፍን መላኩን ጨምሮ የዞንና የከተማ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮቹ ከ246 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን ÷ 75 የፈረስ ጉልበት እንዳላቸው ተመላክቷል፡፡
ቢሮው ከሲንቄ ባንክ ጋር በመተባበር 10 በመቶ ለቆጠቡ ማህበራት ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን እንዳስረከበ ተገልጿል።
ተላልፈው በተሰጡት ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮች 700 ሺህ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር እንደሚቻልም የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ማቲዮስ ሰቦቃ ተናግረዋል።
በክልሉ በበጀት ዓመቱ በአንድ ቢሊየን ብር ለ1 ሚሊየን 40 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን÷ 37 ሺህ ሄክታር መሬት መሰጠቱም ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ ባለፈም ለ66 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል ስልጠና መሰጠቱን ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡
በመቅደስ አስፋውና ጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.