Fana: At a Speed of Life!

በጅማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች በሀገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በጅማ ከተማ በተካሄደው መድረክ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ መንግስታት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀገራዊ የሰላምና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሕብረተሰቡ ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡

መድረኩን የመሩት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ÷ለውጡን ተከትሎ ኢትዮጵያ በርካታ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ፈተናዎች ያለፈች ቢሆንም አሁን ያልተሻገረቻቸው ፈተናዎች ከፊቷ አሉ ብለዋል፡፡

ፈተናዎችን በጥንቃቄ እና በብልሃት ለማለፍ ሕብረተሰብን ያማከለ መፍትሔ ማበጀት ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል።

በተመሳሳይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ዶክተር ለገሰ ከጸጥታ፣ ሙስናና ሌብነት እንዲሁም ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ችግሮቹን ለመፍታት እና በዘላቂነት ለማስወገድ በየደረጃው ያለ የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በእጅጉ እንደሚያስፈልግም ሚኒስትሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.