Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ ላይ የሚመክር ሕዝባዊ ውይይት እየተካሔደ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እና በአፋር ክልል ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ኢብራሂም መሐመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ አሁን የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ እና አስተያየት እያቀረቡ ነው፡፡

ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል÷ በግጭቱ ምክንያትያት የወደሙ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን እና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በልዩ ትኩረት እንዲሠራ፣ የመሰረተ ልማት ተደራሽነትን ጨምሮ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ከሰዓት በርዕሠ መስተዳድሩ እና በሌሎች ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ውይይቱ እስከ ነገ ይቀጥላል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.