Fana: At a Speed of Life!

የማህፀን ውሃ መቋጠር (ovarian cyst) ምንድ ነው?

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህፀን ውሃ መቋጠር (ovarian cyst) እንቁላል የሚመረትበት ቦታ ውሃ ሲቋጥር የሚፈጠር ነው፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት አጠቃላይ ስፔሻሊስት ዶክተር ሸምሴ ሸውሞሎ ብዙ አይነት የማህፀን ውሃ መቋጠር እንደለ ይናራሉ፡፡

እንደ እርሳቸው ገለጻ በጣም የተለመደው ፈንክሽናል ኦቫሪያን ሲስት (Functional Ovarian Cyst) የሚባለው ነው፡፡

ይህም በማህፀን እንቁላል የሚለቀቅበት ቦታ ላይ እንቁላል የዳበረበት ቦታ አለ ፤ እንቁላሉ ሲለቀቀቅ ያ ቦታ በውሃ ሲሞላ የሚከሰት መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡

ይህም በአብዛኛውን ጊዜ በወጣት ሴቶች ላይ የሚታይ እና የህመም ስሜት የሌለው፤ ለሌላ ምርመራ ሲሄዱ በአልትራ ሳውንድ የሚታይ እንዲሁም በሁለት ወር ውስጥ በራሱ ጊዜ የሚጠፋ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የጤና ችግርም የለውም ነው የሚሉት የህክምና ባለሙያው፡፡

ሌላው ፎሊኩላር ሲስት(Follicular Cyst) የሚባለው ሲሆን÷ ይህም እንቁላል እያዳበረ ሲሄድ የተወሰነ ውሃ ይይዝና እንቁላሉ ሳይለቀቅ ሲቀር የሚፈጠር የማሕፀን ውሃ መቋጠር ነው፡፡

ይህም ቀላል አንዳንድ ሴቶች ላይ ብቻ የተወሰነ ህመም የሚኖረው እና በቀላሉ የሚታከም ስለመሆኑም ነው የሚናገሩት።

በሌላ በኩል ደግሞ ተለቅ ያለ እንደ እርግዝና የሆድ መግፋት የሚመሥል እና ህመም ያለው የውሃ መቋጠር (ovarian cyst) እንደሚከሰትም ያስረዳሉ።

ይህ በሚሆን ጊዜም የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የጀርባ ህመም እንዲሁም በግንኙነት ጊዜ ህመም ሊከሰት ይችላል ነው ያሉት፡፡

ሌሎችም እንዲሁ የማህፀን ውሃ መቋጠር ሆነው በውስጣቸው ካንሰር የሚይዙ ይኖራሉ ያሉት ዶክተር ሸምሴ ይህም አብዛኛውን ጊዜ እድሜያቸው በገፋ ሴቶች ላይ የሚታይ ነው ብለዋል፡፡

መሰል ችግሮችም እንደ ደረጃው በጤና ባለሙያ ታይተው በቀዶ ጥገና እና በሌሎች የህክምና ዘዴዎች እንደሚታከሙም አስረድተዋል።

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.