Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል መንግስት የሀገር ውስጥ ገቢ 28 ነጥብ 9 በመቶ ጨምሯል- የፕላን እና ልማት ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት የሀገር ውስጥ ገቢ ካለፈው ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር በ28 ነጥብ 9 በመቶ ጨምሯል ሲሉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ካቢኔያቸው በተገኙበት ያለፉት ስድስት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ የዘርፉ እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ በተሰሩ አበረታች ስራዎች የመንግስት አጠቃላይ ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ28 ነጥብ 9 በመቶ መጨመሩን መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በግማሽ ዓመቱ 172 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች 222 ቢሊየን ማሳካት መቻሉን እና የታክስ ገቢውንም በተመሳሳይ ከታቀደው በላይ መፈጸም መቻሉንም ነው የገለጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.