Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በኢጋድ የፀጥታ ሴክተር ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በምስራቅ አፍሪካ በይነ-መንግስታት (ኢጋድ) የፀጥታ ሴክተር ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ፎረሙ በድንበር ተሻጋሪ የፀጥታ ስጋቶች ዙሪያ ቀጠናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን በፎረሙ ላይ የኢጋድ አምባሳደሮች ኮሚቴ፣ የአባል ሀገራት የፍትህ ሚኒስትሮች እና የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤል ተቋሙን ወክለው በፎረሙ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.