Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች የሥነ-ልቦና እና የንግድ ክኅሎት ሥልጠና መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በጦርነቱ ምክንያት የሥነ-ልቦና፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች ተገቢው የሥነ-ልቦና ፣ የማኅበራዊ ድጋፍ እና የንግድ ክኅሎት ሥልጠና ተጀመረ፡፡

በሥልጠና መርሐ-ግብሩ በደሴና በወልዲያ ከተሞች ለሚገኙ 150 ሴቶች መሰረታዊ የንግድ ክኅሎት ሥልጠና መስጠት መጀመሩን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሚኒስቴሩ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሞድ፥ ሠልጣኞቹ የአምሥት ቀናት ተጨማሪ የንግድ ክኅሎት ሥልጠና እንደሚወስዱ ጠቁመዋል፡፡

ሠልጣኞቹ በመንግስት የተመደበ የሥራ ማስጀመሪያ መነሻ ካፒታል በግለሰብ ደረጃ ወስደው በቅንጅት ለመሥራት በፌዴራል ሚኒስቴር ፣ በክልል እንዲሁም በሰሜን እና በደቡብ ወሎ ዞኖች የሴቶች፣ ሕፃናትና ማኀበራዊ ጉዳይ መምሪያዎች መካከል የውል ስምምነት መፈፀሙም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.