የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 176 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Feven Bishaw

January 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 176 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ፡፡

በዛሬው እለት ከተመለሱት ዜጎች መካከል 1 ሺህ 167ቱ ወንዶች፣ ዘጠኙ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 36 ሺህ 425 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡