Fana: At a Speed of Life!

የሐረር ከተማ ኤሌክትሪክ ፕሮጄክት ትግበራ እየተካሄደ ነው -አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስድስቱ ከተሞች ኤሌክትሪክ ፕሮጄክት አካል የሆነው የሐረር ከተማ ፕሮጄክት ትግበራ በመካሄድ ላይ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡
 
ፕሮጄክቱ በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ አካባቢ በቅርሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት በማያስከትል እና የአካባቢውን መልክዓ ምድራዊ ሁኔታ ባማከለ መልኩ በልዩ ሁኔታ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።
 
ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ በከተማዋ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ እና የኃይል ማነስ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈታ እንደሆነም አቶ ኦርዲን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ ስራውን እየመሩ እና እየፈፀሙ ለሚገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.