Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በግማሽ ዓመቱ 18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የገቢ እና እቅድ ሥራ ሂደት ዳይሬክተር አትንኩት በላይ እንደገለጹት፥ በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ተሰርቷል።

ከመደበኛ ግብር ከፋዮች እና መዘጋጀ ቤት አገልግሎት 22 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር ጠቁመዋል።

ከዚህ ውስጥም በግማሽ ዓመቱ 18 ቢሊየን 280 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ከ343 ሺህ 969 በላይ ግብር ከፋዮች የተገኘ መሆኑን ዳይሬክተሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በዚህም የእቅዱን 81 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው ገለጹት።

የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የግንዛቤ መፍጠር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻሉንም ጠቁመዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ ማቅረብ፣ ያለ ደረሰኝ አገልግሎት እና እቃ መሸጥ እንዲሁም ከዋጋ አሳንሶ ደረሰኝ መቁረጥ የተስተዋሉ ተግዳሮቶች መሆናቸውን አንስተዋል።

ከ467 ሚሊየን በላይ ብር የሀሰተኛ ደረሰኝ ግዢ ያቀረቡ 879 ግብር ከፋዮች
ደረሰኙ ውድቅ እንደተደረገባቸውም አብራርተዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.