Fana: At a Speed of Life!

የነዳጅ ግብይት ሪፎርም ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ውጤት እያስመዘገበ መሆነ ተገለፀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተግባራዊ ከተደረገ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሆነውን የታለመ የነዳጅ ድጎማ አፈፃጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ገምግሟል፡፡

በግምገማውም ሪፎርሙ ይዞት ከተነሳው ዓላማ አኳያ በነዳጅ ድጎማ ምክንያት መንግስት ላይ የነበረውን የእዳ ጫና በመቀነስ፣ በነዳጅ ስርጭት እየተስተዋለ ያለውን ብክነትና ህገወጥነት በማስቀረት ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱ ተመላክቷል፡፡

በትግበራ ሂደቱ የተመዘገቡ ተጠባቂ ውጤቶች እንዳሉ ሆኖ አሁንም በርካታ ችግሮች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን÷ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን በድጎማው ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አንፃር የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸው ተጠቅሷል፡፡

በመድረኩ ውጤታማ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ለችግሮቹ በጥናት ላይ የተመሰረተ መፍትሄ በማበጀት የተጀመረውን የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.