Fana: At a Speed of Life!

የአላቂ ዕቃዎች እጥረት ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት ፈተና ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እያከናወነው ያለውን #የኩላሊት_ንቅለ_ተከላ አገልግሎት የአላቂ ዕቃዎች እጥረት እንደፈተነው አስታወቀ፡፡
በኮቪድ-19 ምክንያት እስከ ተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 141 የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማከናወኑን በሆስፒታሉ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ጸጋዬ ብርሃን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ከመስከረም አጋማሽ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ዘጠኝ የተሳካ ንቅለ ተከላ መከናወኑንም ነው የገለጹት፡፡
በቀጣዩ ሣምንትም ቢያንስ ሁለት ንቅለ ተከላ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሥራዎችን በሚፈለገው ልክ ለማከናወን ቁርጠኝነቱ ቢኖርም የአላቂ ዕቃዎች እጥረት ፈተና ሆኖብናል ነው ያሉት፡፡
ንቅለ ተከላውን ለማከናወን አገልግሎት ላይ የሚውሉ የመድኃኒት፣ የቤተ ሙከራ እና ሌሎች የሕክምና ግብዓቶች አለመኖራቸውንም አብራርተዋል፡፡
እነዚህ ለአገልግሎቱ የሚውሉ ግብዓቶች ቢሟሉ ኮሌጁ የላቀ አገልግሎት እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡
መንግስታዊ እና እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለማዕከሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር በ2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#ስለ_ኩላሊትና_ሽንት_ቧንቧ_ኢንፌክሽን መንስኤ እና ሕክምና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://www.fanabc.com/archives/178233

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.