Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ ምህረቱ ከፋይናንስ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ ምህረቱ ከፋይናንስ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ውይይቱ ባንኩ ከፋይናንስ ተቋማቱ ጋር እንዴት በትስስር እና በቅንጅት መስራት ይችላል የሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንኩ የሰራተኛውን እውቀት በማሳደግ የቴክኖሎጂ እና የዳታ ማዕከሎችን በማሻሻል ረገድ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡

በቀጣይ በተለያዩ ክልሎች ባለመረጋጋት ውስጥ ፈተና ገጥሟቸው የነበሩ ተቋማትን አገልግሎት እንዲጀምሩ መደገፍ ፣ ባንክን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ፣ የክፍያ እና የባንክ ሥርዓት አዋጆችን ማሻሻል ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት የተሻለ እንዲሆን ብሔራዊ ባንኩ ገንዘብን የመቆጣጠር ኃላፊነቱ እንዳለ ሆኖ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ በመሆን እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ባንኮች ራሳቸውን በቴክኖሎጂ በማብቃት እና በማበልጸግ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ እንደሆነ እና ከተደራሽነት አኳያ ግን ቀጣይ ስራዎች እንደሚቀሩ ጠቁመው፥ የኢንሹራንስ እና ባንክ ያልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ላይም የቁጥጥር ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።a

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.