Fana: At a Speed of Life!

የኩላሊት ህመም ማኅበር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሠራተኞች ነፃ ምርመራ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኩላሊት ህመም ማኅበር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሠራተኞች ነፃ የኩላሊት፣ የደም ግፊት፣ የስኳር ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥነ ስርዓት አካሄደ፡፡

ማኅበሩ ምርመራውን እና ግንዛቤ ፈጠራውን ያደረገው÷ ከሄማ አድቫንስድ ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ፣ ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ እና ላብራቶሪ ጋር በመተባበር ነው።

የኢትዮጵያ ኩላሊት ህመም ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ልሳነ ሰይፉ የኩላሊት ህመም ውስብስብ መሆኑን ተናግረዋል።

የደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ ከፍተኛ ውፍረት፣ የዕድሜ መግፋት፣ አልኮል መጠጣት እንዲሁም ሲጋራ ማጨስ ለኩላሊት ህመም አጋላጭ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በመሆኑም ማህበሩ መከላከል ላይ ትኩረት በማድረግ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖር እንደሚሠራ ተናግረዋል።

ጤናማ የአመጋገብ ሥርአትን ማበጀት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ተላላፊ ላልሆኑ የጤና እክሎች ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ተገልጿል።

አትክልትን አዘውትሮ መመገብ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በቀን ከ1 የሻይ ማንኪያ በላይ ጨው አለመጠቀም እና ከ6 እስከ 8 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

#Ethiopia

#ስለ_ኩላሊትና_ሽንት_ቧንቧ_ኢንፌክሽን መንስኤ እና ሕክምና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://www.fanabc.com/archives/178233

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.