የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አልሸባብን እየተዋጉ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

February 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ አካል በመሆን አልሸባብን እየተዋጉ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ተወያዩ።

አልሸባብን ለመዋጋት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ አባል ከሆኑት የመከላከያ ኃይል የጦር መኮኖች ስለሚደረገው የመከላከል ጥረት ገለጻም ተደርጎላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምስራቅ አፍሪካ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በሶማሊያ በሚካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ ሞቃዲሾ መግባታቸው ይታወሳል ፡፡

የመሪዎቹ ውይይት ለቀጣናዊ ችግሮች ቀጣናዊ መፍትሔ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም የአሸባሪውን አልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቀጣናውን ሀገራት ትብብር ማጠናከርን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም የቀጣናው ሀገራት ሽብርተኝነትን ለማጥፋት በጋራ ማቀድ፣ ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ ማሰባሰብና በተለያየ መንገድ ሽብርተኝነትን መዋጋት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!