Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕቅድ፣ የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን ከጎበኙ በኋላ ነው ከርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ጋር የተወያዩት፡፡

በክልሉ የፖለቲካ መረጋጋት፣ የክልሉን ሰላም እና ልማት ለማጠናከር የተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁም የተቋማት ግንባታ ተግባራት አበረታች መሆናቸው በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

የክልሉ መንግስት በክልሉ ከሚገኙት ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ጋር ተባብሮ በመሥራት እያደረገ ያለውን ድጋፍ ቋሚ ኮሚቴው አድንቋል፡፡

አቶ ሙስጠፌ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እና ከፌደራል ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት እየተሠሩ በሚገኙ ሥራዎች ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.