Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀምን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ጋር በመሆን የ2015 ዓ.ም የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀምን እየገመገሙ ነው፡፡

በግምገማው ላይ የካቢኔ አባላቱና የሚመሯቸው ተቋማት ከተሰጣቸው ተልእኮና በእቅድ የያዙትን ተግባራት ከመፈፀም አኳያ፣ የከተማዋን  የህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ከመመለስ አንጻር የነበረው ሂደት በዝርዝር እየቀረበ ነው፡፡

በተጨማሪም በህብረተሰቡ ውስጥ የሚታዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከማቃለልና ከመፍታት አኳያ የነበረው ሂደትና ፋይዳ በዝርዝር እየታየ እንደሚገኝ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.