Fana: At a Speed of Life!

በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የተገነባው የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ዛሬ ተመረቀ፡፡

በቻይናው ሲ ሲ ኢ ሲ ሲ ተቋራጭ የተገነባው ወደቡ በ34 ነጥብ 1 ሔክታር ላይ ማረፉ ተገልጿል፡፡

የድሬዳዋ ወደብ ከዚህ ቀደም ከኢትዮ ጅቡቲ በውሰት በወሰደው 0 ነጥብ 5 ሄክታር ላይ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን የወደቡ ዋና ስራ አስፈፃሚ ገልፀዋል፡፡

የደረቅ ወደብ እና ተርሚናሉ የሀገሪቱን የገቢ እና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ለሁለንተናዊ የምጣኔ ሃብት ዕድገትና የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

ወደቡ በአንድ ጊዜ 140 ተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ፣ ሁለት የዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን እንዲሁም ወደቡን ከኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር የሚያገናኝ የባቡር ሃዲድ ተገንብቶለታል፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አዲስ ብራንድ ይፋ ተደርጓል።

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.