Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ለወደሙ 71 ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ሙሉለሙሉ ከወደሙ ትምህርት ቤቶች የ71 ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ÷ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በዚህ አመት ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅና ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መማር ማስተማር እንደሚደርሱም ተናግረዋል፡፡

ግንባታቸው ከሚጀመረው ትምህርት ቤቶች ውስጥ 50ዎቹ በአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍና በትምህርት ሚኒስቴር፣16ቱ ደግሞ በሰዎች ለሰዎች ድርጅት እንዲሁም 5ቱ ትምህርት ቤቶች በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የሚገነቡ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

“አዲስ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች” የሚል ዲዛይን መጠናቀቁን የተናገሩት ሚኒስትሩ ደረጃቸውን የጠበቁ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ዲዛይን ነው ብለዋል።

በቀጣይ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች በአዲሱ ዲዛይን እንደሚገነቡም ነው የተገለጸው፡፡

እስካሁን ከተለያዩ አካላት ለትምህርት ቤቶች ግንባታ 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.