Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በበጋ የመስኖ ስንዴና በአትክልት ልማት አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በበጋ የመስኖ ስንዴና በአትክልት ልማት አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪና የክልሉ ካቢኔ በክልሉ ኤረር ወረዳ በበጋ መስኖ ልማት እየለማ ያለን የስንዴና የአትክልት ማሳ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት አቶ ኦርዲን በድሪ÷ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ካሉት አበይት ተግባራት መካከል የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በገጠር ወረዳዎች በአርሶ አደሩ ተነሳሽነት እየተከናወኑ ያሉ የበጋ የመስኖ የስንዴና የአትክልት ልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ያለው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም ባሻገር በገበያ ላይ የሚስተዋለውን የስንዴ አቅርቦት ፍላጎት እንደሚያሟላ አመላክተዋል፡፡

የግብርና ስራውን ለመደገፍና በገጠር ወረዳዎች የሚነሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርናና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው÷ በክልሉ ከ4 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ልማት ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.