Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሥድሥት ወራት 5 ሺህ 606 ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሥድሥት ወራት 5 ሺህ 606 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
 
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ግርማ ባይሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በተያዘው በጀት ዓመት 11 ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ታቅዶ ነው ወደ ስራ የተገባው፡፡
 
አሁን ላይም በክልሉ በአጠቃላይ 10 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡
 
ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በአግባቡ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ዘንድም በክልሉ ያለውን የቅድመ መደበኛ ትምህር ቤት ቁጥር ለመጨመር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በዚህ መሰረት ባለፉት ሥድሥት ወራት በህዝብ ተሳትፎ 6 ሺህ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገባንት ታቅዶ 5 ሺህ 606 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
ከዚህ ውስጥም አሁን ላይ 5 ሺህ 522 የሚሆኑት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ነው ሃላፊው ያስረዱት፡፡
 
በግንባታ ስራው የክልሉ ባለሃብቶች ፣ የእምነት ተቋማት፣ ነዋሪዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት መሳተፋቸቸውን ጠቅሰዋል፡፡
 
በቀጣይም በክልሉ በሁሉም ቀበሌ ገበሬ ማህበር እና ከተሞች ወቅቱን ያገናዘቡ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በቅንጅት እንደሚሰራም ነው የተናገሩት።
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.