Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በሶማሊኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የወር ስያሜዎች ስራ ላይ እንዲውሉ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሶማሊኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የወር ስያሜዎች ስራ ላይ እንዲውሉ አፅድቋል፡፡

የሶማሌ ክልል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የክልሉ የተለያዩ የክልሉና ሌሎች ባለሞያዎች በሶማሊኛ የወር ስያሜዎች ላይ ባካሄዷቸው ጥናቶች ላይ በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ ባለሞያዎቹ በሶማሊኛ ቋንቋ በቀን፣ በወርና በዓመት ላይ የተከናወነውን ጥናት የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በሶማሊኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የወራት ስያሜዎችን አድንቀው ፥ ይህም የሶማሊኛ ቋንቋን ለማሳደግና ለመጠበቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።

ኮሚቴው በክልሉ የትምህርት ሥርዓትንና የትምህርት ተቋማትን የሚቆጣጠረው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሶማሊኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማሳደግ እያከናወነ የሚኘውን ስራዎች ኮሚቴው ማበረታታቱን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

በዚህ መሠረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የሚከተሉትን የሶማሊኛ ቋንቋ የወር ስያሜዎች ከዛሬ ጀምሮ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አስተላልፏል ።

1. ኮድሂን/መስከረም/September

2.ዲሪር / ጥቀምት/October

3. ጉድባ / ህዳር/November

4.ሆሬይ /ታህሳስ/December

5.ደርበለይ / ጥር/January

6. አሪር/ የካቲት/February

7. ኡር /መጋቢት/march

8. ዱጋቶ /ሚያዚያ/april

9. ሚአድ/ግንቦት/may

10.አጋሊ/ ሰኔ/june

11. አፍጋል/ሀምሌ/july

12.ነፍ/ነሀሴ/augest

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.