Fana: At a Speed of Life!

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ በልዩ ክትትል እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽሕፈት ቤት ባለቤትነት የማስፋፊያ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የተቀናጀ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ግንባታው የሚካሄድበት ቦታ ውኃማና ረግረጋማ በሆነው ፍል ውሃ አካባቢ በመሆኑ በቁፋሮ ሥራው ላይ ውኃ ሞልቶ ሥራውን ከተጠበቀው በተለየ ሁኔታ አስቸጋሪ ማድረጉ፣ መነሳት የነበረበት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት (ትራንስፎርመር) በወቅቱ አለመነሳቱና ለማንሳት ረዘም ያለ ሂደት መውሰዱ እንዲሁም በግንባታው ማረፊያ ቦታ ላይ መፍረስ የነበረበትን ሕንጻ በጊዜው አለመፍረሱ በእክልነት ቀርበዋል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት የባከነውን ጊዜ ለማካካስም የፕሮጀክቱ መደበኛ የሥራ ሰዓት 16 ሰዓት ቢሆንም እስከ 24 ሰዓት ድረስ በማራዘም በግንባታ ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች በመፍታት ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡

መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ውል ተገብቶ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም የቦታ ርክክብ መደረጉን በአዲስ አበባ ከተማ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠሪ እና ተቆጣጠሪ የሥነ ሕንጻ ባለሙያ ነጋሽ መሐመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራ በአግባቡ መጀመሩንም ነው የገለጹት፡፡

540 ቀናት እንደሚጨርስ ኮንትራት የተያዘለት ይህ ፕሮጀክት እስካሁን ከተጀመረ ሦስት ወራት አስቆጥሯል፡፡

በእስካሁኑ ክንውኑም የፊዚካል አፈጻጸሙ አምስት በመቶ እንዲሁም የፋይናንስ አፈጻጸሙ ሁለት በመቶ ገደማ መድረሱን ነው የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ያብራሩት፡፡

ለፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገደማ እንደተበጀተለትም ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.