Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል 12 አይነት መደበኛ ክትባቶች እየተሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ 12 አይነት መደበኛ ክትባቶች እየተሰጡ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ክትባት ዴስክ ሃላፊ መልካሙ አያሌው እንደገለጹት÷ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ በትግራይ ክልል ለህጻናት አስፈላጊ የሆኑ ክትባቶችን ለማዳረስ በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
 
ለዚህም ወደ ትግራይ ክልል የተላከው የጤና ሚኒስቴር የባለሙያዎች ቡድን ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
በቀጣይ የሚሰጠው መደበኛ ክትባት በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች እንዲዳረስም ከዩኒሴፍ፣ ከዓለም ጤና ድርጅ እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
 
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የኩፍኝ በሽታ ክትባት በትግራይ ክልል ለማስጀመርም አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በተለይም የሃብት ማሰባሰብ፣ የግንዛቤ ፈጠራ፣ የባለሙያዎችን ስልጠና፣ የመድሃኒት ማከማቻ ማዕከላት፣ ፍሪጅ እና ሌሎች ግብዓቶችን የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
በቅርቡ የሚጀመረው የየብስ ትራንስፖርትም በክልሉ የሚሰጡ የተለያዩ ክትባቶችን ወደ ክልሉ ለመላክ እና ለማሰራጨት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡
 
 
በመላኩ ገድፍ
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.