የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ መሰረተ ልማት ጎበኙ

By Mikias Ayele

February 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ መሰረተ ልማት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እየተሰሩ ያሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የህብረተሰቡን ችግር እየቀረፉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ተጀምረው ያልተቋጩ የድልድይና የመንገድ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ርዕሰ መስተዳድሩ መመሪያ ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ አብርሃም ማርሻሎ እና ከፍተኛ የክልል የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡