Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ስርዓቶች ውስጥ ማካተት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የትምህርት ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ስርዓቶች ውስጥ ማካተት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳኤንል በቀለ ፈርመዋል፡፡

የስምምነቱ ዋና አላማ ሁለቱም ተቋማት ያለባቸውን የጋራ ሃላፊነት ለመወጣት እና የሰብዓዊ መብት እሴቶችን ወደ ማህበረሰቡ ማስረጽ ለማስቻል ነው ተብሏል።

ይህን ስምምነት ትምህርት ቤቶችም በመደበኛው እና ከመደበኛው ውጭ በሆነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውንም መግለጫው አመላክቷል።

ስምምነቱ የሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለው ነው ዋና ኮሚሽነሩ ያነሱት።

በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲጣሱ የሚስተዋሉ የሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩበትና በሰብዓዊ መብት ውጤታማ ለመሆንም በትምህርት ስርዓቱ እንዲካተት መድረጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ በበኩላቸው÷ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንዲሁም መብትና ግዴታውን የሚያውቅ ዜጋ ለመፍጠር ስምምነቱ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብለዋል።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.