Fana: At a Speed of Life!

996 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ ከሳኡዲ አረቢያ  ዜጎችን የመመለስ ስራ 996 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 996 ዜጎች መካከል 987 ወንዶች ሲሆኑ 9ኙ ደግሞ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በኤርፖርትና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ 38 ሺህ 449 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችነ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.