Fana: At a Speed of Life!

በሽግግር ፍትኅ ሥርዓቱ አፈጻጸም ዙሪያ ለአውሮፓ ኅብረት አምባሳደሮች ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሽግግር ፍትኅ ሥርዓቱ አፈጻጸም እና በኢትዮጵያ ስለተመደቡት የዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለሙያዎች ኃላፊነት ያላትን አቋም ለአውሮፓ ኅብረት አምባሳደሮች ግልፅ አደረገች፡፡

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፍትኅ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸውም በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና ተጠያቂነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥርት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢፌዴሪ ፍትኅ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ÷ ኢትዮጵያ በፕሪቶሪያ የተፈረመውን ሥምምነት እና ቀጣይ የአፈፃፀም ማዕቀፎች ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.