Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በኢኮኖሚ ጠንካራ ሆና እንድትቀጥል አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመን ቢሮ “ኢትዮጵያ ታምርት፤ ኦሮሚያ ታምርት፤ ሸገር ታምርት ” በሚል መሪ ሀሳብ አምራች ኢንዱስትሪውንና የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማነቃቃት ከባለሀብቶች ጋር የንቅናቄ መድረክ በሸገር ከተማ አስተዳደር እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ሀገር በኢኮኖሚ ጠንካራ ሆና እንድትቀጥል እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን መፍጠር እንዲቻል አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር በመፍታትና ለዘርፉ ትኩረት ለመስጠት በመላ ሀገሪቱ እየተተገበረ የሚገኝ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባሳለፍነው አመት መጀመሩን አስታውሰዋል።

ንቅናቄው ከተጀመረ በኋላም በዘርፉ ለውጦች መታየታቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ ለአብነትም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ስራ አቁመው የቆዩ 200 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት መግባታቸውን በማስታወስም፥ ዘርፉ ውጤታማ ሆኖ ለሀገር አስተዋፅኦ እንዲያበረክት አመራሩና ባለሀብቱ ተቀራርቦ በመስራት የዘርፉን ችግሮች መቅረፍ ይገባል ነው ያሉት።

በሸገር ከማ አሰተዳደር ከ4 ሺህ በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መኖራቸው ተጠቁሟል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.