Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ከተማ ከ260 በላይ ሕገ-ወጥ ማኅተሞች እና ሃሰተኛ ሠነዶች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 01 ከ260 በላይ ሕገ-ወጥ ማኅተሞችንና ሃሰተኛ ሠነዶች መያዛቸው ተገለጸ፡፡

ሃሰተኛ ማኅተሞቹና ሠነዶቹ የተያዙት ስታር ተብሎ በሚጠራው ኅንፃ ተከራይተው የማተሚያ ቤት ሥራ ሲሰሩ በነበሩ ግለሰቦች ነው፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን መልካሙ መንግስት ÷ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ሥር አውለው አስፈላጊውን ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከተሠሩት ኅገ-ወጥ የማጭበርበሪያ ማኅተሞች መካከል በዋናነት ÷ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፣ የከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ፣ የመሬት አስተዳደር፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን መንገድ ትራንስፖርት ፣ የከተማው የሁሉም ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች ፣ የቀበሌ ማኅበራዊ ሸንጎዎች፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የተለያዩ የግል ኮሌጆች እና የሌሎች በርካታ መሥሪያቤቶች ማኅተሞች ይገኙበታል፡፡

ሕገ-ወጥ ሠነዶችን በተመለከተ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ፣ የቦታ ፕላን፣ የተሽከርካሪ ሊብሬ፣ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ የቀበሌ መሸኛ፣ የቀበሌ ማኅበራዊ ሸንጎ ማስረጃ እና ሌሎች በርካታ ሠነዶች እንደሚገኙባቸው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.