ስፓርት

ተጠባቂው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዘመ

By Mikias Ayele

February 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዝሟል ።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት በ12ኛ ሳምንት የሊጉ ተስተካካይ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ለጊዜው ባልተገለፀ ምክንያት ነው ወደ ሌላ ጊዜ እንደተላለፈ የተገለፀው።

በነገው ዕለት እንዲደረግ መርሐ-ግብር ተይዞለት የነበረው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታን በተመለከተም  እስካሁን የተባለ ነገር የለም ሲል የዘገባው ሶከር ኢትዮጵያ ነው።