Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ ለአደጋ ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር  በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ማህበሩ የመጪውን የበልግ ወቅት የአየር ፀባይ አዝማሚያ ትንበያን በተመለከተ በአዳማ ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በምክክር መድረኩ የማህበሩ ዋና ፀሀፊ አቶ ጌታቸው ታዓ እንደተናገሩት÷  የአየር ንብረት ቅድመ ትንበያ እና ቅድመ እርምጃን በመከተል ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ከባለድርሻ አካላት ጋር  ማህበሩ በቅንጅት እየሰራ ነው፡፡

በዚህም በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የጎርፍ አደጋ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሰዊና ወረዳ ድርቅ እንደሚከሰት ቀድሞ መተንበይ እንደተቻለ አንስተዋል፡፡

በነዚህም አካባቢዎች በማህበረሰቡ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንደተቻለም አቶ ጌታቸው ታዓ መናገራቸውን ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው÷ የበልግ ወቅት የአየር ፀባይ አዝማሚያ ትንበያን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራው ስራ ተስፋ ሰጪ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ወደፊትም በሚሰሩ ስራዎች ይበልጥ በመቀናጀት በተፈጥሮ አደጋ የሚከሰቱ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል የሚደርሰውን ምጣኔ ሀብታዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን ቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.