Fana: At a Speed of Life!

ካለፉት አባቶች በጎ ነገሮችን በመቅሰም ለኢትዮጵያ ሰላም በጋራ ልንቆም ይገባል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ካለፉት ጀግኖች አባቶቻችን በጎ ነገሮችን በመቅሰምና በመሰነቅ ለኢትዮጵያ ልማትና ሰላም በጋራ ልንቆም ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

የንጉሥ ሚካኤል 173ኛ ዓመት የልደት በዓል በንጉሡ የትውልድ ቦታ መቅደላ ወረዳ ደብረ ዘይት ከተማ ተከብሯል፡፡

አቶ ደመቀ በአከባበር ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ብትቆይም በሕዝቡ አጋርነትና በመንግሥት ቁርጠኝነት በመልካም የዕድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

አባቶች ለሀገራቸው ሉዓላዊነት ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ እንደተዋደቁ ሁሉ÷ የአሁኑ ትውልድም ያለ ልዩነት ለኢትዮጵያ ብልጽግና በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡

ሰላምና ጸጥታን ማስከበር፣ የኢትዮጵያን ዕድገት ማስቀጠል፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስና የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ በየደረጃው መመለስ የመንግሥት ተቀዳሚ ሥራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

እንዲሁም አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የተገነባውን ጤና ጣቢያ መርቀው ከፍተዋል፡፡

 

በሙሉቀን አበበ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.