ስፓርት

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀመራል

By Tamrat Bishaw

February 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡

የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቀጣይ ውድድሩ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንዲሁም ከ14ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎችን መካሄጃ ከተማና ስታዲየም በተመለከተ የስራ አመራር ቦርዱ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህ መሰረትም ውድድሩን በድሬደዋ ወይም ባህር ዳር ከተማ ለማከናወን የፊታችን ሰኞ ሜዳዎቹን የሚገመግም ኮሚቴ የሚልክ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ማክሰኞ ዕለት ከሁለቱ የተመረጠውን ሜዳ በተመለከተ ውሳኔ እንደሚተላለፍ እና የሊግ ውድድሩም የፊታችን ቅዳሜ የሚጀመር መሆኑ ተመላክቷል፡፡