Fana: At a Speed of Life!

የደም ሕክምና ፍላጎት እና አቅርቦት አልተጣጣመም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደም ሕክምና ፍላጎት እና አቅርቦት ያለመጣጣም ችግር መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 228 ሺህ ዩኒት ደም ለማሰባሰብ ቢታቀድም ማሰባሰብ የተቻለው ግን 167 ሺህ 850 ዩኒት ደም ብቻ ነው፡፡

መፈጸም የተቻለው የዕቅዱን 75 በመቶ መሆኑ የሚያሳየው የደም ሕክምና ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣሙን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

በክረምት ወቅት የትምህርት ተቋማት መዘጋት እንዲሁም በዓላት በሚበዙበት እና በጾም ወቅት በቂ የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሽ አለመገኘቱ በምክንያትነት ተነስቷል፡፡

በጥቅምት፣ ሕዳር እና ታኅሣሥ የደም ለጋሹ ቁጥር መሻሻል ቢያሳይም በጥር ከትምህርት ቤቶች ለእረፍት መዘጋት እና በዓላት መብዛት ጋር ተያይዞ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሹ ቁጥር መቀዛቀዙን ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለመድረስ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች በንቃት ደም እንዲለግሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለዚህም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለከተሞች በሚገኙ ተንቀሳቃሽ ቡድኖች፣ በቀይ መስቀል ግቢ እና ጎማ ቁጠባ አካባቢ በሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ግቢ ባለው ደም ባንክ፣ በሁሉም ክልሎች በ43 የደም ባንኮች ደም መለገስ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

የደም እጥረት አጋጥሞ በደም እጦት ምክንያት ሕይወት እንዳይጠፋ ህብረተሰቡ በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገስ የሌሎችን ሕይወት እንዲታደግ የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.