የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

April 07, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኮቪድ-19 ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለሚያስከትለው ቀውስ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ስለማጠናከር መወያየታቸውም ነው የተገለጸው፡፡