የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል የሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የድምፅ አሠጣጥ ተጀምሯል

By Mekoya Hailemariam

February 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ህዝበ ውሳኔ እየተካሄደ ነው።

በክልሉ ስር በሚገኙ÷ የጋሞ፣ ጎፋ፣ ዎላይታ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶና፣ ደቡብ ኦሞ ዞኖች በተጨማሪም በቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ እና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ሕዝበ ውሳኔው እየተካሄደ ነው።

በሕዝበ ውሳኔው ላይ 5 ሺህ 274 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች ይሠማራሉ መባሉን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቦርዱ በክልሉ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ባካሄደው የመራጮች ምዝገባ÷ 3 ሚሊየን 28 ሺህ 770 ሰዎች ድምፅ ለመስጠት መመዝገባቸውንም አሳውቋል፡፡

ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ሰዎች ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

 

በማቱሳላ ማቴዎስ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television