Fana: At a Speed of Life!

ትውልድን ለማፍራት የሚሰሩ ትምህርት ቤቶች ላይ መንግስት በትኩረት ይሰራል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልድን ለማፍራት የሚሰሩ ትምህርት ቤቶች ላይ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በደሴ ከተማ  የሚገኙ የተለያዩ  የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝታቸውም ÷ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የማለፊያ ውጤት ከፍተኛ ነጥብ የተመዘገበበትን የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

አዳሪ ትምህርት ቤቱ እንደ ሀገር ያስመዘገበው ውጤት የሚበረታታ  መሆኑን የገለጹት አቶ ደመቀ ÷መንግስት ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በቀጣይ አዳሪ ትምህርት ቤቱ የተሻለ ስራ እንዲሰራ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ነው ያረጋገጡት፡፡

በተመሳሳይ አቶ ደመቀ መኮንን የወሎ ተርሸሪ ኬርና የማስተማሪያ ሆስፒታልን የጎበኙ ሲሆን ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ከዚህ በላይ እንዳይዘገይና በቴክኖሎጂ ልቆ እንዲሰራ መደረግ እንዳለበት ጠቅሰው÷ ገንዘብ ሚኒስቴርና የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮጀክቱን መደገፍ ይገባቸዋል ብለዋል።

ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ይጠይቃል ተብሏል።

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.