Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ቱርክ ዛሬ ጠዋት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ለደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም በፍጥነት እንዲያገግሙ መመኘቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከአደጋው ጋር በተያያዘ ለሚያስፈልገው ድጋፍ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት እና ህዝብ ጎን እንደምትቆምም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.