Fana: At a Speed of Life!

5 ቢሮዎችን በጋራ የሚይዘው የትራንስፖርት ዘርፍ ዋና መ/ቤት ግንባታ በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1 ነጥብ 575 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አምስት ቢሮዎችን በጋራ እንዲይዝ ታስቦ እየተገነባ የሚገኘው የትራንስፖርት ዘርፍ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክትን በቀጣዩ ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ በ4 ሺህ 300 ካሬ ሜትር ላይ የሚገነባው የትራንስፖርት ዘርፍ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 52 ነጥብ 93 መድረሱ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ከመሬት በታች ሦስት፣ ከመሬት በላይ ደግሞ 20 ወለሎች እንዳሉት በአዲስ አበባ ከተማ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት የትራንስፖርት ዘርፍ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ተጠሪ እና ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ታደለ ዳንደና ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅ ለሕዝብ ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ ለአሽከርካሪዎች እና የተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች ማረጋገጫ ባለስልጣን፣ ለትራፊክ አስተዳደር ባለስልጣን፣ ለአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ እና ለትራንስፖርት ፕሮግራም አስተዳደር ቢሮ አገልግሎት ይውላል ተብሏል፡፡

በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር 2020 የተጀመረው ፕሮጀክቱ በቀጣዩ ዓመት እንዲጠናቀቅ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

መሬትን ጨምሮ ወደታች ያሉ ወለሎች 210 ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ማቆም እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለ 3 ሺህ የሴክተር ባለስልጣን ሠራተኞች ቢሮዎች፣ ጂምናዚየም እና ስፓ፣ ለሕጻናት ማቆያ ቦታ፣ ለትራንስፖርት ዘርፍ ሙዚየም፣ ለሞዴሎች እና የምስል ማሳያዎች፣ ለሕዝብ ምግብ ቤት (302 መቀመጫዎች) እና ለሠራተኛ ካፍቴሪያ (350 መቀመጫዎች) እንደሚኖሩት ነው የተገለጸው፡፡

ለመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና እርዳታ መስጫ፣ ለዲጂታል ቤተ መጻሕፍት ለእያንዳንዱ ሴክተር ቢሮ፣ ስድስት ትናንሽ የመሰብሰቢያ አዳራሾች እና አራት የስልጠና ማዕከላት፣ አንድ መካከለኛ የኮምፒውተር የላቀ ማዕከል እና ለአምስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጋራ ቦታ ይኖሩታል ነው የተባለው።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.