Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ አኒ ዳሳጉፐታ እና ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በትብብር ሊሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

አጋርነትን በማጠናከር ትብብርን ወደ ስትራቴጂክ እና የተቀናጀ ደረጃ ለማሳደግ እንዲሁም የአዲስ አበባን ቀጣይ የልማት ስትራቴጂካዊ ፍኖት ለመንደፍ፣ የተቀናጀ መረጃን መሰረት ያደረገ የአመራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የመረጃ ቋት ለመገንባት ዳይሬክተሯ እንደሚደግፉም ተናግረዋል።

እንዲሁም አዲስ አበባን የነገ ተስፋ የሆኑ ህጻናትን በእንክብካቤ ለማሳደግና ለትውልድ ግንባታ የምትመረጥ ከተማ ለማድረግ የተሰነቀውን ራዕይ ሁለገብ በሆነ መልኩ ለመደገፍ መስማማታቸውንም አስታውቀዋል።

የልዑካን ቡድኑ ላሳየው ትብብር፣ ፈቃደኝነትና ተነሳሽነት ከንቲባ አዳነች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.