የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካው የማዕድን ኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

By Alemayehu Geremew

February 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው በአፍሪካ የማዕድን ዘርፍ ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ በሚል በተዘጋጀው መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በመርሐ-ግብሩ ዓለምአቀፍ የማዕድን ኩባንያዎች፣ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማትዮስ ተካፋይ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉባዔው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የማዕድን ሚኒስትሮች የአፍሪካ የማዕድን ሐብት አጠቃቀም እንዲሁም ቀጣይ ትብብርን በተመለከተ ሰፊ የውይይት ሃሳብ አንስተው መምከራቸው ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታው በቆይታቸውም በኢትዮጵያ ማዕድን ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው ዓለም አቀፍ የማዕድን ተቋማት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመርሐ-ግብሩ በኢትዮጵያ የሚገኙ የማዕድን አምራች ኩባንያዎች መሳተፋቸውም ተመላክቷል፡፡