Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሠራዊት ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶችን ሊመክት የሚያስችል የሪፎርም ስራ መስራቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል ሪፎርም መስራቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመከላከያ ሚኒስቴርን የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትን እየገመገመ ነው ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በግምገማው መከላከያ ሠራዊት ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል ሪፎርም መስራቱን አንስቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ሪፖርትና መስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ከህብረተሰቡ የተነሱ ጉዳዮችን ያቀረበ ሲሆን÷ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂን ጨምሮ የተቋሙ አመራሮች ምላሽ መስጠታቸውን የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.