Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ የማስተዋወቅ ስራ በፈረንሳይ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በፈረንሳይ ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የተመራ የልዑካን ቡድን በፈረንሳይ ሀገር እየተካሄደ በሚገኘው በዓለም አቀፉ የጨርቃጨርቅ አመታዊ ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ ፈረንሳይ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ በአመታዊ ኤክስፖው ላይ ከዓለም አቀፍ የዘርፉ አምራቾችና ገዢዎች ጋር በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች የማስተዋወቅና የባለሃብቶችን ተሳትፎ አስመልክቶ የማስተዋወቅ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በአመታዊ ኤክስፖው ከተለያዩ ሀገራት የተመረጡ ከ900 በላይ በአልባሳት እና ጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ምርት የታወቁ አምራች ድርጅቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች፣ የዘርፉ ዓለም አቀፍ አንቀሳቃሾች እና የምርት ገዢዎች እንደሚሳተፉ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለም አቀፉ የጨርቃጨርቅ ኤክስፖ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 እንደሚቆይ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.