Fana: At a Speed of Life!

1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት ለህብረተሰቡ ተሰራጨ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከጅቡቲ የገዛውን ፓልም የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ አጓጉዞ ለህብረተሰቡ እያሰራጨ መሆኑን አስታወቀ፡፡

እስካሁን ከ1 ሚሊየን 196 ሺህ በላይ ሊትር ዘይት ለህብረተሰቡ መሠራጨቱን እና ሥርጭቱ አሁንም እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከ5 ሚሊየን እና በሁለተኛው ዙር ከ16 ሚሊየን 518 ሺህ በላይ ሊትር ዘይት ግዥ ተፈጽሟል ተብሏል፡፡

በዚህም በመጀመሪያው ዙር የተገዛው ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ሲሆን የደረሰው ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የመጀመሪያው ዙር የምግብ ዘይት የማጓጓዝ ሥራ በቀጣዩ ሣምንት እንደሚጠናቀቅ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ተወካይ መስፍን መለሰ አረጋግጠዋል፡፡

ንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባከናወነው ድልድል መሰረት÷ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር እና ሲዳማ ክልሎች እያሰራጨን ነው ብለዋል አቶ መስፍን፡፡

ሽያጩም የገንዘብ ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ የአንድ ሊትር ዘይት ዋጋ የትራንስፖርቱን ሳይጨምር በ104 ብር ከ66 ሣንቲም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት÷ ለአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች፣ ለአማራ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ሐረሪ እና ሶማሌ ክልሎች እየተሰራጨ መሆኑን የኮርፖሬት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቀጸላ ሸዋረጋ ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.