የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Feven Bishaw

February 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ።

የክልሉ የ2015 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈጻጻም ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

በዚህም ወቅት በበጀት አመቱ ግማሽ ዓመት 1 ቢሊየን 273 ሚሊየን 197 ሺህ 387 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ቢሊየን 77 ሚሊየን 330 ሺህ 361 ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 85 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ372 ሚሊየን 504 ሺህ 850 ብር ወይም የ53 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

ገቢው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ከወረዳዎችና ከከተሞች የተሰበሰበ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡